ሐበሻ ወደ ሰሜን ሸዋ የመጣበት ዘመን
☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆
ከጥንት ጀምሮ እስከ 1800 ዓ.ም ድረስ ሰሜን ሸዋ በየጁ ስርዎ መንግሥት በራስ ጉግሣ አያት አገዛዝ ስር ነበረች፡፡ ጉግሣ የመርሶ ባሬንቱ ልጅ ነዉ፡፡ ከ809-1813 በነበሩት ዓመታት የአማራ ዘር ወሰን ሰገድ (የ ንጉስ ሣህለ ሥላሴ አባት) ከትግሬ ገዥ ከራስ ወልደ ሥላሴ ጋር ተባብረዉ በሃይማኖት ጦርነት ራስ ጉግሣን ወግተዉ ከአሸነፉ በኋላ ነበር ሰሜን ሸዋን ተቆጣጠሩ፡፡ ሐበሻ ዘር ወደ ሰሜን ሸዋ የመጣዉ በዚህ ወቅት ነበር፡፡ ወሰን ሰገድ ሰሜን ሸዋን ከያዘ በኋላ ቤተክርስቲያን ማቋቋም ጀመረ፡፡ በደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤክርስቲያን፤ በደብረ ሊባኖስ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን እንዲሁም በሰላን ድንጋይ ቤተክርስቲያናትን አቋቋመ፡፡ ቤተክርስቲያን የሐበሾች መቂያ ካርድ ነች፡፡ ከ16ኛ ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የዉጭ መንግሥታት የኢትዮጲያ ገዥ መደቦችን በምክር በፖለቲካ በኢኮኖሚ በጦር መሣሪያ የሚደግፉት በክርስትና ሃይማኖት ምክንያት ነዉ፡፡ ኦሮሞ ዘለዓለም እየተጨቆነ የሚኖረዉ እስላም ተብሎ ነዉ፡፡ የምኒልክ ቅድመ አያት ወሰን ሰገድ ቤተክርስቲያን ማቋቋም በጀመረበት ወቅት ከሰሜን ሸዋ ሙስሊሞች ከፍተኛ ተቃዉሞ ገጠመዉ፡፡ ሙስሊሞች አድመዉ የወንድ ወሰን ሚስት እንደተኛች በአንኮበር ቁንዶ በሚባል ቦታ የተሰራ መኖሪያ ቤቱን አቀጣሉበት፡፡ ልጁ መርእድ አዝማች እናቱን ከቤት ለማዉጣት ሲሄድ በጬቤ ደረቱ ተወግቶ ጥቂት ቀናት ከቆየ በኋላ ሞተ፡፡መርእድ አዝማች ከሞተ በኋላ የወንድ ወሰን 8ኛ የመጨረሻ ልጅ ሣህለ ሥላሴ የአባቱን ሥልጣን ተረከበ፡፡ ሣህለ ሥላሴ ከ1813-1847 የሰሜን ሸዋ ንግሥ ተብሎ ነገሠ፡፡ ሣህለ ሥላሴ ከእንግሊዝ በተሰጠዉ መድፍ በሸዋ ኦሮሞ ላይ ተኩስ በመማር ከ4000 በላይ ሕዝብ የፈጀ መሆኑን ታሪክ ይመሰክራል፡፡ ሣህለ ሥላሴ ኃይለ መለኮትን ወለደ፡፡ኃይለ መለኮት ሚኒሊክን ወለደ፡፡
ይቀጥለላል.
Jabaadhu seenaa gaaridha
ReplyDelete