አወይቱ /𝘼𝙬𝙬𝙚𝙚𝙩𝙪
ሰንበቴ ከተማ በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከአዲስ አበባ 260 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ አነስተኛ ከተማ ናት፡፡ ከዚች ከተማ የሰንበቴን ወንዝ ተከትለን 4 ኪ.ሜ እንደተጓዝን እንፋሎት የሚተፋውን የአወይቱ ፍል ውሃ እናገኛለን፡፡
አወይቱ በሰንበቴ እና አጣዬ ወንዞች መካከል ድንቅ መልክዓ ምድራዊ ውበት ባለበት ቦታ መገኘቱ እና በአለቶች መካከል የሚነሳው ሙቅ የእንፋሎት ጭስ ሁሌም ጎብኝዎችን ያስደምማል፡፡ በሞቃታማው እንፋሎት ለመታጠን እና አካባቢውን ለመጎብኘትም ብዙዎች ወደ አወይቱ ይመጣሉ፡፡ የተፈጥሮ እንፋሎቱ አካላዊ መዝናናትን ከመፍጠር ባሻገር ከበሽታ ለመፈወስና አልፎ አልፎም ምግብ ለማብሰል ጥቅም ላይ ይውላል፡፡
No comments:
Post a Comment